טֶבַע וּסְבִיבָה
מיחזור
מיחזור, קיימות ושימוש חוזר הם מונחים שהפכו לחלק מהחיים שלנו. במשחק המופלא, קופסה יכולה להפוך למכונית, שמיכה ישנה יכולה להיות אוהל ועוד כיד הדמיון הטובה. דרך היצירה והפעלנות, ילדים לומדים להשתמש במשאבים לצרכים שונים, ובכך מיישמים באופן מעשי את עיקרון הקיימות. את הסקרנות, היוזמה, היצירתיות והבנת החשיבות של שימוש חוזר במשאבים, אפשר להגביר ולעודד דרך ספרים שמבליטים נושאים אלו.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለንባብ የሚሆኑ ጠቃሚ ቤተሰባዊ ምክሮች
በንባብ መጀመሪያ ላይ ልጆች የፊደሎችን ቅደም ተከተልና የቃላትን ፍሰት ለመከተል ብዙ ጥረት ያደርጋሉ። የቅርብ ታላላቆች ሲያነቡላቸው ሲያዳምጡ ከልፋታቸው ራሳቸውን ነጻ ማድረግ፣ ምናብ ውስጥ መግባትና በመፅሃፍ ውስጥ አዳዲስ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ። በእርግጥ ልጆቹ በራሳቸው እንዲያነቡ ማበረታታት ይመከራል። ግን በተመሳሳይ ጊዜ አብረው ማንበብን በጋራ እንዲቀጥሉ ይሆናል።
ውይይት- ከተሞክሮ መማር
አንድን ነገር ለመገንባት ወይም ለማቀድ ሞክረው ግን እንዳሰቡት ያልሆነ ነገር አጋጥሞዎታል? እኛ እንዳሰብነው ሳይሆን ሲቀር ምን ይሰማናል? እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ ምን ሊረዳዎ ይችላል?
ሁልጊዜ ያልተሳኩ ሙከራዎችዎንና ለመቋቋም የሚረዳዎትን ነገር ከልጆች ጋር መጋራት ይችላሉ።
የQR ኮድ
ከካን ሃስኬቲም ኮርፖሬሽን፣ ከግሪንስፎን እስራኤል ፋውንዴሽንና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ያርዴንና ዲዲ በፒጃማ” ከሚለው ክፍል “አስደናቂ ሃሳብ” የሚለውን ክፍል ያዳምጡ።
በጋራ መገንባት
መጀመሪያ ሲያቅዱና ሲገነቡ ምን ይከሰታል? ያለ እቅድስ ሲገነቡ? እርስዎ በሚሰበስቡት ነገሮች በሌጎ ብሎኮች ወይም በቤትዎ ውስጥ ባሉ ማናቸውም ነገሮች እገዛ ሁለቱንም የመገንባት መንገዶች በመሞከር ምን እንደተሰማዎት ብሎም በእያንዳንዱ ጊዜ ውጤቱ ምን እንደነበረ ይመልከቱ።
ምናባዊ ምስል
የምናብና የስዕል ጨዋታ መጫወት ይችላሉ። ከቤተሰብ አባላት አንዱ ለሌሎቹ ይገልፃል፡- በዓይነ ህሊናዬ የሆነ ነገር አያለሁ… ያለው ነገር… ሲሆን በ… ቀለም የሆነ – ሌሎች ተሳታፊዎችም በመግለጫው መሰረት ይሳሉ። በእያንዳንዱ ሥዕል ላይ ምን ያያሉ? በጣም የሚስብ!
ውይይት
በቤትዎ ውስጥ ምን ይወዳሉ? በቤት ውስጥ የሚኖረውስ ማነው? ታሪኩን ተከትለው ከልጆች ጋር ስለ ቤትዎ ማውራት ይችላሉ፤ ምንና ማን በውስጡ እንዳለ፦ የቤተሰብ አባላት፣ የቤት እንስሳት፣ ተወዳጅ አሻንጉሊቶችና ሌላስ ማን? (በአንቀጹ መጀመርያ ላይ የታየ ነው)
ሌላ ተጨማሪ ሳይሆን ሳጥን
“ይሄ ቤት ማለት በጠቅላላው የሚኖሩበት ሳጥን ነው…” ኮዱን ስካን ያድርጉና በዳቲያ ቤን ዶር የተጻፈውንና የተቀናበረውን ዘፈን ይቀላቀሉ።
ጨዋታ - ድብብቆሽ
የት መደበቅ ይገባል? – እንደ ያስሚንና እናቷ ታዳጊው ሕጻን ሲደበቅና ወላጁ ሲፈልገው እርስዎም ድብብቆሽ መጫወት ይችላሉ። ተሳካ? – ተጨማሪ ዙር መጀመርና ቤተሰብ አባላትን ማሳተፍ ይችላሉ።
እኛም እየገነባን ነው
እርስዎም ከሣጥን ቤት መሥራት ይችላሉ። የሚያስፈልገው ትልቅ የካርቶን ሳጥን፣ ነፃ ጊዜና ጥሩ ስሜት ብቻ ነው። አሁን እርስዎ በገነቡት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ጓደኞችን መጋበዝ ይችላሉ። ትንሽ ሳጥን ብቻ ነው ያገኙት? – ወደ አሻንጉሊቶች ቤት መቀየር ይችላሉ።
የካርቶን ሳጥን
ምርጥ ጓደኛሞች
በጣም አስደናቂው ነገር
የቤት ውስጥ ገጠመኝ
ማሽኑ
