טֶבַע וּסְבִיבָה
חורף וגשם
השמיים משנים צבעים... שלוליות, גשם, חלזונות, מטריות ומעילים - החורף הגיע!
בעזרת הספרים בנושא חורף תוכלו לחגוג את חילופי העונות, לשמוח עם הגשם הראשון ולשים לב לטבע ולסביבה המשתנים בחורף.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ውይይት– ሐኑካችን
የሐኑካ በዓል በዓለም ዙሪያ ባሉ አይሁዶች በትውልዶች ሁሉ ይከበራል። በበዓል ወቅት ስለ ቤተሰብዎ ወጎች ማውራት ይችላሉ – ምን ዓይነት ልማዶች አሉዎት? በአላስካ ካሉ የሐኑካ ልማዶች ጋር እንዴት ይመሣሠላሉ? ባልተለመደ ሁኔታ ወይም ልዩ ቦታ ላይ አክብረው ያውቃሉ?
ከውጪ ባለ ብርሃን - ከውስጥ ባለ ብርሃን
በታሪኩ ተመስጦ ምሽት ላይ መውጣትና በዙሪያዎ ያሉትን ብርሃኖች ማየት ይችላሉ፦ ኮከቦችን፣ ጨረቃን፣ የመንገድ መብራቶችንና ምናልባትም የሐኑኪያ መብራቶችን ይመልከቱ – ምን ያህል መብራቶችን ይመለከታሉ? ውጪ ለምታገኟቸው እያንዳንዱ የብርሃን ምንጭ የሚያስደስትዎ፣ የሚያበረታዎ ወይም ለሕይወትዎ ብርሃንን የሚያመጣ ነገር ላይ መናገር ይችላሉ።
ሐኑካ በዓለም በሁሉም ቦታ
ዛሬ ሻማዎችን የት ማብራት ይፈልጋሉ? በእሥራኤል ውስጥ ልዩ ቦታ ላይ? በሰሃራ በረሃ? ወይስ ምናልባት በበረዷማዋ አላስካ ውስጥ? በየእለቱ በተለየ ቦታ እያከበሩ እንደሆነ የሚያስቡበት የዓለም ካርታ መስራትና አስደሳች ጨዋታ መጫወት ይችላሉ! በዙሪያዎ ያለው ምንድን ነው? ከፓንኬኮችና ዶናት በተጨማሪ ምን ይበላሉ? በበዓሉ ላይ ምን ዓይነት የሀገር ውስጥ ልማዶችን ይጨምራሉ?
ሰሜናዊው ብርሃን
የመጽሐፉን ምሥሎች በመመልከት በማርከሮችና በባለቀለም እርሳሶች አንድ ላይ ለመሳል መነሳሳትና የራስዎን አስደናቂ የሰሜናዊ ብርሃንን መፍጠር ይችላሉ።
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር የዓረፍተ ነገር ድግግሞሽ
ብዙዎቹ የህፃናት መፃህፍት ታዳጊዎቹ ታሪኩን እንዲከታተሉና በንባብ እንዲቀላቀሉ የሚረዳ ተደጋጋሚ ዓረፍተ ነገር አላቸው። በልዩ ድምጽ በመታገዝ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ወይም የንባብ ፍጥነትን በመቀየር በማንበብ ጊዜ የተደጋገመው ዓረፍተ ነገር አጽንዖት ሊሰጠው ይችላል። ለምሳሌ፡- “ከእኛ ጋር ና” ሲል የሚጋብዝ የእጅ ምልክት ማከል ወይም የዓረፍተ ነገሩን መጨረሻ ማራዘም ይችላሉ፦ “እኛም ዘንድ ቦ-ታ አለን”።
ጓደኞችን ማስተናገድ
በመጽሐፉ ውስጥ ያለችው ልጅ ልጆቹን ወደ ዣንጥላ እንዲመጡና ከእርሷ ዘንድ “እንዲስተናገዱ” ትጋብዛለች። ልጆቹን በቤታቸው ማስተናገድ እንደሚፈልጉና ማንን ማስተናገድ እንደሚፈልጉ መጠየቅ ይችላሉ።
ታዳጊዎች እቤት ውስጥ ሲያስተናግዱ አንዳንድ ጊዜ ጨዋታቸውን ማካፈል ይከብዳቸዋል። በዚህ ላይ ተወያይተው በመጽሐፉ ውስጥ እንዳለው ዣንጥላ ልጅቷ ወደ መጽሐፉ እንዲገቡ ስትጋብዝ የልጅቷ ሆኖ እንደሚቀረው ሁሉ የግል ንብረታቸውም የእነርሱ እንደሆነ ማስረዳት ይችላሉ።
የQR ኮድ
ከ”ደስ የሚል ቢራቢሮ” ፕሮግራም ላይ ዘፈኑን በካን ሒኖኺት ማዳመጥ ይችላሉ። ዘፈኑን በድምጽና በእንቅስቃሴ መቀላቀል ይችላሉ። ግጥምና ዜማ፦ ዳቲያ ቤን ዶር ኦፕሬተር፦ አስቴር ራዳ፣ ኡሪ ባናይ፣ ሜታል ራዝ፣ አሚ ዌይንበርግ።”
ቤተሰብና ዣንጥላ
በአንድ ዣንጥላ ስር ስንት የቤተሰብ አባላት ሊገቡ ይችላሉ? በብርድ ልብስስ ስር ምን ያህል? በመመገቢያ ጠረጴዛው ስርስ? በመፅሃፉ ተነሳሽነት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በደስታና በሳቅ እንዴት ሁላችሁ በጋራ መሰባሰብ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይችላሉ።
የዝናብ ላይ የእግር ጉዞ
ዝናባማ በሆነ ቀን ራስዎን በቦት ጫማዎች፣ ኮትና ዣንጥላ ያስታጥቁና በዝናብ ውስጥ ለመራመድ ይውጡ! ወደ ኩሬዎቹ ውስጥ ገብተህ በዝናብ ጊዜ በአካባቢው የሚለዋወጡትን ልዩ ነገሮች መመልከት ትችላለህ – ምን ያህል ሰዎች ውጪ አሉ? ሰማዩ ምን ይመስላል? ዝናቡ መሬት ወይም ንጣፍ ጋር ሲገናኝ ምን ይሆናል? በአየር ውስጥ ምን ሽታ አለ?
መነጋገር - ማን ሊያግዝ ይችላል?
ሁሉም ሰው ሌሎችን ታዳጊ ሕጻናትን እንኳን ሳይቀር ሊያግዝ ይችላል። ታዳጊ ሕጻናቱን ሌሎችን በምን እንደሚያግዙ መጠየቅ ወይም በሚከሰትበት ጊዜ እንደሚረዷቸው መንገር ይችላሉ፦ “ጠረጴዛውን ለማዘጋጀት እንደረዳኸኝ አስታውስ?”፣ “መጫዎቻዎቹን ለማዘጋጀት እንዴት እንደረዳሽኝ ተመልከቺ!”
ታሪኩን ማዳመጥ
“ኖኒና እናቱ” የሚለውን ታሪክ ማዳመጥ ይፈልጋሉ? – የQR ኮዱን ስካን ያድርጉና የታሪኩ የድምጽ ቅጂ ላይ ይደርሳሉ። በሚያሽከረክሩበት ጊዜ፣ በሚጫወቱበት ወይም አብረው ተቀምጠው መጽሐፍ በሚያገላብጡበት ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ።
ታሪኩ በምስል
ስዕሎቹ የታሪኩ አካል ሲሆኑ በእነርሱ አማካኝነት ታዳጊ ሕጻናቱ የታሪኩን ሂደትና ዝርዝሮቹን ያውቃሉ፤ ያስታውሳሉም። ስዕላዊ መግለጫዎቹን አንድ ላይ በማየት ኖኒ ለእናቱ የሰጣትን ዕቃዎች መፈለግ ይቻላል። ‘ቦርሳ የተሳለበት ቦታ የት ነው?’ እና ‘የኮት ምስል የት አለ?’
ጨዋታ - የእቃዎች ግንብ
በእናት ላይ በተቆለሉ ነገሮች በመጠቀም በተራ የእቃዎችን ግንብ መገንባት ይችላሉ፦ በጥንቃቄ አንዱን በሌላው ላይ በማድረግ ኩቦችን፣ መጫወቻዎችን፣ ኮፍያዎችን፣ ቦርሳዎችንና ማከል የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ማስቀመጥ ይችላሉ።
ውይይት - ችግርና መፍትሄ
ችግር ሲያጋጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ? – እናንተው ወላጆች የገጠማችሁን ችግር ለሴቶችና ወንዶች ልጆች ማጋራት ትችላላችሁ። ምን እንደተሰማችሁ እንደገና ለማጠንጠን ሞክሩ፤ ሊሆኑ ስለሚችሉ መፍትሔዎችም አብራችሁ አስቡ። ከዚያም ችግሩ እንዴት እንደተፈታ ተርኩ።
በ... ምን ሊደረግ ይችላል?
የተፈለገው መሪ ወይም ሳህን ወይም … ሊሆን ይችላል – ኮዱን ስካን በማድረግ ስለ ፈጠራ ቪዲዮ ማየት ይችላሉ! ከዚያ አንድ ላይ ማሰብዎን ይቀጥላሉ – በጥቅልል ወረቀት ምን ሊደረግ ይችላል? በመሃረብስ? በድንክዬ አሻንጉሊትስ?
በጋራ መዘመር
ድንክዬዎቹ እንጉዳዮችን በመትከል “የሚያውቋቸውን ሁሉንም ዘፈኖች ዘምረዋል” – እርስዎም የሚወዷቸውን ዘፈኖች አንድ ላይ መዘመር ይችላሉ። ስለ ድንክዬዎቹ፣ ስለ ዝናብ ወይም ስለሚያበረታታዎትና ስለሚያስደስቱዎት ዘፈኖች መዘመር ይችላሉ።
ጨዋታ - እኔ የትኛው ድንክዬ ነኝ?
በእያንዳንዱ ዙር ከተሳታፊዎቹ አንዱ በመጽሐፉ ውስጥ የሚታየውን ድንክዬ ሆኖ ይተውናል- ጥላ የያዘውን ድንክዬ፣ እንጉዳይ የሚተክለውን ድንክዬ ወይም በኩሬ ውስጥ የሚዘለውን ድንክዬ። ሌሎቹ ተሳታፊዎች ድንክዬው ምን እየሰራ እንደሆነ መገመትና በመጽሐፉ ገፆች መካከል ማግኘት አለባቸው።
ሐኑካን በአላስካ
አንዲት ልጅና አንድ ዣንጥላ
ኖኒ እና እናት ከመዋዕለ ህጻናት በመጓዝ ላይ ናቸው።
ስለ ድንክዬዎች፣ እንጉዳዮችና ሌሎችም መጽሐፍ
ምስል
