טֶבַע וּסְבִיבָה
שמחה במה שיש
פעמים רבות במהלך החיים, ההתמקדות במה שאין לנו מונעת מאתנו לראות את היופי ואת השפע שהם מנת חלקנו. הכרת הטוב היא בסיס לראיית העולם באופן חיובי ואופטימי. הספרים שלפניכם מעודדים אותנו לראות את העושר שלא ניתן לקנות בכסף, להוקיר את הטוב בחיינו ולהודות על מה שיש.
סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ይህንን እንዴት ማንበብ ይችላሉ?።
ልጆች የመጽሐፉን ያልተለመደ መዋቅር እንዲረዱና እንዲደሰቱ ለመርዳት እራስዎን “ተጫዋቾች” እንዲሆኑ ይፍቀዱ። የተራኪውን ሚና ሲወጡ መደበኛና ወጥ የሆነ ዜማ ይያዙ። ሉዊን ሲሆኑ ስሜታዊ ልምዱን ለማጎልበት የድምጽና የሰውነት ምልክቶችን ይጠቀሙ – የሪቫው ቀለም ሲያቀልመው በመገረም ከእርሡ ጋር ይናደዱ፤ በተስፋ መቁረጥ ጊዜ ቲያትራዊ ትንፋሽን ይጨምሩ።
ታሪካችን ሲቀየር
ሊቆጣጠሩት ከማይችሉት ተለዋዋጭ እውነታ ጋር ከልጆችዎ ጋር መነጋገር ይችላሉ። “ይህ በእርሥዎ ላይ ቢደርስ ምን ይሰማዎታል?” “ተመሳሳይ ነገር ተሰማዎት?” በልጅነት ያጋጠሙዎትን የግል ልምዶች ማካፈል ልጆችዎ ርኅራኄ እንዲሰማቸውና ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋል።
የራሥዎን ታሪክ መፍጠር
የራሥዎን ታሪክ መፍጠር
ኮዱን ስካን ያድርጉና በታሪክ ሳጥኑ እንዴት እንደሚጫወቱ በማወቅ የራሥዎን ታሪኮች ይፍጠሩ! ሳጥኑ ለመታተም ዝግጁ ሲሆን በቀላሉ ይቁረጡ፣ ይለጥፉትና ይደሰቱ።
መሣያ ጥርብ ድንጋይ
በወረቀት ላይ በውሃ የተበጠበጠ ቀለም ቦታ ይፍጠሩ ወይም ሁለት ወረቀቶችን አንድ ላይ በትንሹ የውሃ ቀለም መጠን በመካከላቸው ያስቀምጡ። ያልተጠበቀ ቅርጽ ይፍጠሩ። የቀለመው ሲደርቅ ከእርሱ አዲስና አስገራሚ ነገር ለመፍጠር ይሞክሩ።
ውድቀትን መቋቋም
ቤት ውስጥ “የመንገድ እንቅፋት” መፍጠር ይችላሉ። እያንዳንዱ ሰው ተራ በተራ ለማለፍ እየሞከረ ሌላ ፈተና ሲጨመርበት:- ለምሳሌ ትምህርቱን በማለፍ ወለሉን በመወልወያ እየጠረገ ወይም በጀርባው ላይ እቃ ተሸክሞ መሄድ ይችላሉ። ከ‹‹እንቅፋት›› ውስጥ አንዱን ያጋጠመው ሰው ወደ ኋላ ተመልሶ እንደገና ይጀምራል።
ምክር ለቤተሰባዊ ንባብ
በመፅሃፍ ውስጥ ያለው ተደጋጋሚ ዓረፍተ ነገር ልጆች ታሪኩን እንዲከታተሉ፣ በንባብ ንቁ እንደሆኑ እንዲሰማቸውና የጋራ ልምዳቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳል። የተደጋገመውን ዓረፍተ ነገር በልዩ ድምጽ ማንበብ፣ የእጅ ምልክቶችን መጨመር ወይም የንባብ ፍጥነትን መለወጥ ይችላሉ። በዚህ መንገድ ወደ እርሱ በመጡ ቁጥር ሴትና ወንድ ልጆች ከእርስዎ ጋር በመገናኘታቸው ደስተኞች ይሆናሉ።
ይሄንም ያንንም
ይሄንም ያንንም የመፈለግ አዝማሚያ በልጆች ሕይወት ውስጥ የታወቀ ሁኔታ ነው – ከልጆችዎ ጋር መነጋገርና መጠየቅ ይችላሉ:- ወይዘሮ በጻልኤል የያዙትን እቃዎች ሁሉ ለምን ጣለች? የገዛችውን ሁሉ የምትፈልገው ይመስላችኋል? ይህ ሲከሰት ምን የተሰማት ይመስላችኋል? ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞዎታል? ወይዘሮ በጻልኤል ምን እንድታደርግ ይመክራሉ?
ጥንቃቄ! እንዳትወድቁ!
ምን ያህል አሻንጉሊቶችና እቃዎች ሳይወድቁ በእጆችዎ ውስጥ መያዝ ይችላሉ? በታሪኩ ተነሳሽነት አሻንጉሊቶችን፣ መጫወቻዎችን (የማይሰበሩ)፣ ትራሶችንና ለስላሳ እቃዎችን ከቤት ውስጥ መሰብሰብና ከአንድ ነጥብ ወደ ሌላ መንገድ ማዘጋጀት ይችላሉ። አሁን እያንዳንዱ ሰው ተራ በተራ በተቻለ መጠን ብዙ እቃዎችን በመያዝ በተሠየመው መንገድ አብሮ ይራመዳል – የወደቀ ነገር አለ? ወደ መጀመሪያው ይመለሱ።
ምን ያህል መልካም ነው!
ምን ነገር መልካም ያደርግልዎታል? በቀኑ መጨረሻ ከመተኛቱ በፊት “ምን ያህል መልካም ነው” የሚለውን ጨዋታ መጫወት ይችላሉ – እያንዳንዱ ሰው ዛሬ ስለተፈጠረ ጥሩ ነገር ወይም ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ ነገር ይናገራል።
የምንም ሳጥን
እናንተም የራሳችሁ ነጻ ሳጥን ሊኖራችሁ ይችላል። የሳጥን ወይም የካርቶን ቦርሳ በመውሰድ በወረቀት፣ ሥዕሎች፣ ተለጣፊዎችና ጌጣጌጦች አስጊጡት። በደበራችሁ ጊዜ ሳጥኑን በመክፈት ምናባችሁን ተጠቅማችሁ በዚህ ጊዜ ምን እንደሚይዝ መወሰን ትችላላችሁ። ምናልባት የኳስ ጨዋታ የምትጫወቱበት በ“ቢሆን” የምትጫወቱበት ምናባዊ ኳስ ይኖረው ይሆናል። ምናልባት አብራችሁ የፈጠራችሁት ምናባዊ ታሪክ ወይም እናንተ የምትወስኑት ሌላ ፈጠራ ሊሆን ይችላል።
ውይይት - መምረጥና ማዋል
ስለ ሲሪልና ጦብያ ምርጫ መወያየት ተገቢ ነው- በእርስዎ አስተያየት ለምን ሁሉንም ወርቅ ላለመጠቀም የመረጡ ይመስልዎታል? አስገርሞዎታል? በእርስዎ አስተያየት ለምን ወርቁን በትምህርት ላይ ለማዋል መረጡ?
ስዕላዊ መግለጫዎች– ፍየሏ የት አለች?
ፍየሏ በሙሉ ታሪኩ ውስጥ ከሲሪልና ጦብያ ጋር አብራ ትሄዳለች። በመጽሐፉ ስዕላዊ መግለጫዎች ውስጥ ፍየሏን መፈለግ ይችላሉ፦ ምን እየሰራች ነው? ከቤተሰብ ጋር ያላት ግንኙነት ምን ይመስላል? ከፍየሏ እይታ አንጻር ታሪኩን ለመናገር ይሞክሩ – በመጽሃፉ ውስጥ ምን ይገጥማታል?
ጨዋታ– ሃብቱን መፈለግ
ለቤተሰብ አባላት መስጠት የሚፈልጓቸውን ትንንሽ ስጦታዎች ይሰብስቡ፦ ስዕል፣ ቡራኬ ወይም እቃ። በተራው መሰረት ከቤቱ አባላት አንዱ የራሱን ስጦታ ይደብቃል። ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም ሀብቱን በምልክቶች ይፈልጉታል፡- “ቅርብ-ሩቅ”፣ “ትኩስ-ቀዝቃዛ” ወይም በቤቱ ዙሪያ የተበታተኑ ቀስቶች።
ፍጹም ስጦታዎች
የራስዎን የቤተሰብ አባላት ምን ያህል ያውቃሉ፣ እና ለእነሱ ፍጹም ስጦታ የሚሆነው ምን ይመስልዎታል – የሚገዙት ነገር ወይስ የልምድ ስጦታ፣ ለምሳሌ፦ አብራችሁ የምታሳልፉት ጊዜ፣ ወይም ምናልባት የሆነ ቦታ የሚደረግ ጉዞ ነው? ጨዋታ ስለመጫወት እና ስለማወቅስ? በእያንዳንዱ ዙር፣ ሁሉም ተሳታፊዎች አንድ ተሳታፊ እንደ ስጦታ ምን ማግኘት እንደሚፈልግ ለመገመት ይሞክራሉ። ግምታቸው በጣም ቅርብ የሆኑት ያሸንፋሉ… ፍጹም የቤተሰብ እቅፍ።
ውይይት
ደስ የማይሉ ነገሮች በሁላችንም ላይ ይከሰታሉ – ግን የሚከሰተው በእኛ ላይ ብቻ ነው ወይ? አንድ ደስ የማይል ነገር ሲከሰት፣ የሚፈጠሩትን ስሜቶች መወያየት እና ሊረዱ የሚችሉ ሰዎችን እንዲያስቡ እንዲሁም አንዳቸው ሌላውን እንዲረዱ እና አንዳቸው ሌላውን እንዴት ማበረታታት እንደሚችሉ ለመወያየት ይፈልጉ ይሆናል።
ማብራሪያዎች ታሪክ ይናገራሉ
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ማብራሪያዎች ቃላት ሳይጠቀሙ በዊንስተን ጓደኞች ላይ ምን እንደተፈጠረ ይነግሩናል። ዊንስተን ብቻ አያስተውለውም። አንድ ማብራሪያ ምረጥ፣ የዊንስተንን ጓደኛ በቅርበት ተመልከት እና እንደነሱ ሆነው ታሪካቸውን ይንገሩዋቸው፡- እነርሱ ምን እየተሰማቸው ነው? እነርሱ ምን እያሰቡ ነው? ትኩረትዎን የሳበው ይህ ልዩ ማብራሪያስ?
እንደእድል ሆኖ አጋጠመኝ!
በብሩህ ጎን ለማየት መሞከር ይፈልጉ ይሆናል! በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ላይ፣ የደረሰብዎትን መልካም ነገር ለቤተሰብዎ ያጋሩ – ወላጆችም ልጆችም ስለ ዉሎአቸው ዜና ማጋራታቸውን ያረጋግጡ።
ማን ያስደስተኛል? እና ማን ያስገርመኛል?
ማብራሪያዎችን ባንድነት ተመልከቷቸው እና የሚያዝናናዎትን ዝርዝሮች ይፈልጉ – እያንዳንዳችሁ ምን የሚያስደስት ነገር አገኛችሁ? ከዝርዝሮቹ ውስጥ የትኛው አስገረምዎት?
ታላቁ ሽልማት
ሻልኬቱ
የሚያስደንቅ ምስቅልቅል ታሪክ
የከዋክብቱ ዛፍ
ከባሥሊኤል ጎዳና የመጣችዋ አንዲት ሴት
ድመቱ ሻኡል
የሆነነገር
የምንም ስጦታ
ጣቢያው
ሰባቱ መልካም ዓመታት
ፍጹሙ ስጦታ
ዊንስተን ተጨነቀ
