סְּפָרִים
ታሪኩን ተከትለው የሚመጡ ቤተሰባዊ ተግባራት፡-
ጠቃሚ ምክር ለቤተሰባዊ ንባብ
አንዳንድ ጊዜ ታዳጊዎች መጽሐፍን ለማንበብ በተለያዩ ምክንያቶች እምቢ ይላሉ። ለማንኛውም መጽሃፍ እንዲማሩ ልናደርጋቸው የምንችለው እንዴት ነው? መጽሐፉን እራስዎ ካገላብጡና ዓይንዎን የሚስቡ ወይም የሚያዝናናዎትን ዝርዝር ነገሮች ቢጠቁሙ የማወቅ ጉጉታቸውን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ። መጽሃፎቹን በሚደረስበትና በሚታይ ቦታ ያስቀምጡና እርስዎና ልጆችዎ በምቾት አብረው ለመቀመጥ በሚችሉበት ጊዜ ትክክለኛውን የንባብ ጊዜ ለማግኘት ይሞክሩ።
ለተጨማሪ ሐሳቦች የፒጃማ ቤተ መፃህፍት ድረ ገጽን ይፈልጉ – “ልጆችን በመጻሕፍት እንዴት እንደሚስቡ”
የሚፈልጉትን ሳይቀበሉ ሲቀሩ
ልጁ ውሻ ሳይሆን ድመት ሲያገኝ ምን የተሰማው ይመስልዎታል? የሆነ ነገር ፈልገው በምትኩ ሌላ ነገር እንዳገኙ አጋጥሞዎት ያውቃል? የምንፈልገውን በትክክል ሳናገኝ ስንቀር ምን ማድረግ እንችላለን?
እንስሳትን መመልከት
በመጽሐፉ ውስጥ ልጁ የድመቱን ልዩ ገፅታዎች ይገነዘባል፦ ጉልበቱ ላይ ይዘላል፣ ይልሰዋል፣ ይቸበችበዋል፣ ይከረክራል። በአካባቢዎ ያሉትን እንስሳት በጋራ መከታተልና የእያንዳንዱን እንስሳ ልዩ ገፅታዎች ለመለየት መሞከር ይችላሉ – እንዴት ይንቀሳቀሳል? ምን ድምጾች ያወጣል? ለሰዎች ምን ምላሽ ይሰጣል?
ማስመሰልና መገመት
ልጁ አንድ ድመት በሰርፕራይዝ ተቀብሏል – ሌላ ምን አስገራሚ እንስሳ ወደ ቤት “መግባት” ይችላል? አዞ በሶፋ ላይ እንዴት ይቀመጣል? ምንጣፍ ላይ እባብ እንዴት ይሳባል? አንድ ጨዋታ መጫወት ይችላሉ፦ አንዱ ድምጽ ያስመስላል ሌላኛው ደግሞ ይገምታል።
ለቤተሰባዊ ንባብ የሚሆን ጠቃሚ ምክር
ይህ አንድ ማየት የተሳነው ወይም ዓይነ ስውር ወንድም ስላለበት አንድ ልዩ ቤተሰብ የሚገልጽ ልዩ መጽሐፍ ነው። ተራኪው ወንድም በቤተሰቡ ውስጥ ያሉትን ችግሮችና በቤት ውስጥ የሚፈለግበትን ውስንነት ጠንቅቆ እያወቀ ነገርግን ዓለምን በአዎንታዊ መልኩ ይመለከታል። ንባቡንና ውይይቱን ከመጽሐፉ ልዩ ይዘት ጋር ለማስተካከል ለእናንተ ወላጆች ከጋራ ንባቡ በፊት መጽሐፉን እንድታነቡ እንመክራለን።
ውይይት
በታሪኩ ውስጥ ያለው ልጅ እድለኛ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን? በምን እድለኛ ናችሁ? ወላጆችና ልጆች እርስ በርሳችሁ እንደ ቤተሰብ አብረው በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች በተመለከተ ማካፈል ትችላላችሁ። በሳምንት አንድ ጊዜ የቤተሰቡ አባላት ባለፈው ሳምንት ያጋጠሟቸውን አወንታዊ ነገሮች የሚያካፍሉበት መደበኛ ሥርዓት መፍጠር ትችላላችሁ።
ምን ታያላችሁ...?
ዓይነ ስውራን ልጆች ሕይወትን እንዴት ይለማመዳሉ? ኮዱን በማድረግ ከዓይነ ስውራን ልጆች ጋር “ለጥያቄው ይቅርታ” የሚለውን ክፍል ማየት ትችላላችሁ። ከቪዲዮው በኋላ መወያየት ጠቃሚ ነው፦ ሕይወታችን እንዴት ተመሳሳይ ነው እንዲሁም በቪዲዮው ውስጥ ካሉት ልጆች እንዴት ይለያሉ?
ድጋሜ በማንበብ ምን እናውቃለን?
በሁለተኛው ንባብ አዳዲስና አስገራሚ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል። ምስሎችን በመመልከትና የሃጋይን የእይታ እክል ፍንጭ በመፈለግ መጽሐፉን ሁለት ጊዜ ማንበብ ተገቢ ነው፦ ቃላቱና ምስሎቹ ስለቤተሰብ ፈተና ምን ፍንጭ ይሰጣሉ? በመጀመሪያው ንባብ ይህን አስተውላችኋል?
ምናባዊ ጨዋታ
ሃጋይ ምናባዊ ታሪኮችን እንዴት እንደሚናገር ያውቃል። እናንተም ሞክሩት! ሁለት እቃዎችን በመምረጥ ምናባዊ ታሪክን ለመተረክ ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ -ብሩሽና ምንጣፍ፣ ጠርሙስና የድመት አሻንጉሊት፣ ኮፍያና መስኮት – እናንተ በጋራ ባሰባሰባችሁት ምናባዊ ታሪክ ውስጥ ምን ሊደርስባቸው ይችላል?
ድመት ውሻ አይደለም!
ምን ዓይነት እድል ነው!
